የንጉሥ እራት መርሃ ግብር በአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት
የንጉሥ እራት መርሃ ግብር በአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት
የኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህክምና ማህበር በአፋር ለሚገኙ በጦርነቱ ለተጎዱ የማህበረሰቡ ክፍሎች የህክምና አገልግሎቶችን ፈጸመ።
በአጠቃላይ ከ 500 በላይ ተፈናቃዮች በጭፍራ መጠለያ ጣቢያ የሕክምና ርዳታ እና 900 ቤተሰቦች የአልሚ ምግብ አግኝተዋል።
900 ካርቶን አልሚ ምግብ ታድሏል።
ለ 32 የሚደርሱ የ ኤችአይቪ ሕሙማን በልዩ ሁኔታ/ ከህጻናት ውጭ የአልሚ ምግብ ተጠቃሚ ተደርገዋል።
የየቤት ለቤት ጉብኝት በማድረግ ወደ 27 የሚጠጉ የወለዱ አራሶች ታይተዋል።
የተሟላ የ OR team ( anesthesiologist, plastic surgeon, orthopedics and OR nurses) ይዘን በመሄድ 4 ህሙማን የቀዶ ህክምና ተደርጎላቸዋል (major surgeries)
ከ 50 በላይ ህሙማን በ ፊዚዮትራፒ ቡድን ታይተዋል።
የ ተረፈንን መድሃኒት ለጭፍራ ተፈናቃዮች ጤና ጣቢያ ለ ሲስተር ሰሚራ የጤ/ሃላፊ አስረክበናል።
በቀዶ ጥገና በኩል የተረፉ ግባአቶች በዶር ዳዊት በኩል ለዱፍቲ ሆስፒታል አስረክበናል።
የኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የህክምና ማህበር በአፋር ለሚገኙ በጦርነቱ ለተጎዱ የማህበረሰቡ ክፍሎች የሰጡትን አገልግሎት በተመለከተ ለሸገር ራዳዮ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።
Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association (EOTMA) is a nonprofit organization established by Ethiopian Orthodox Tewahedo healthcare professionals.
Support war-affected Ethiopians by working with us. You can simply purchase very essential medical supplies and we will take care of the shipping and distributing materials.
Select from these selections and on the checkout simply select EOTMA address for shipping.
Learn more about Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በመሆን በሀገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚፈልጉ ዳያስፖራ ባለሀብቶችን የሚያበረታታ እና ግንዛቤ የሚያሳድግ ፎረም አዘጋጁ።
ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሠጡት መግለጫ ፎረሙ ጥር 3 ስራ የሚጀምር ሲሆን፥ ጥር 6 ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ፎረሙ ጥር 3 በይፋዊ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚጀመር እና በቀጣይ ቀናትም የተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩት ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፥ ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን የማፍሰስ ዕቅድ ያላቸው ዳያስፖራ ባለሐብቶች በፎረሙ እንዲሳተፉ እና ከኢንቨስትመንት ማኅበረሰቡ፣ ከኮሚሽኑ የፌዴራል እና የክልል እንዲሁም የከተማ አሥተዳደር ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር እንዲመክሩ ብሎም የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲመለከቱ ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡
በኢንቨስትመንት መሰማራት እና በዕድሉ መጠቀም የሚፈልጉ ባለሐብቶች investethio.com የሚለውን የኮሚሽኑን ድረ ገጽ መመልከት እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡
Via: FBC
፩ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው እንዲመጡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሃገራቸውን ምርቶች ሊተዋወቁ እና ለመግዛት አመቺ ሁኔታን መፍጠር የሚችል የባዛር እና ኤግዚቢሽን በእንጦጦ ፓርክ ለህዝብ ክፍት ሆኗል።
የዳያስፖራ አባላት በመዲናዋ ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ በቂ ዝግጅት ተደርጓል
********************************
ወደ አገር ቤት የገቡ የዳያስፖራ አባላት በሚንቀሳቀሱባቸው ሥፍራዎች ሁሉ የጸጥታ እና ደህንነት ስጋት እንዳይገጥማቸው ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
‘የአንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ አገር ቤት’ ጥሪ ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት በመግባት ላይ ናቸው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ የዳያስፖራ አባላቱ በመዲናዋ ያለ ምንም ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከአየር መንገድ ጀምሮ በሚያርፉባቸው ሆቴሎች፣ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በንግድ ማዕከላት፣ በትራንስፖርት እና ሌሎች ሥፍራዎች ሳይታወኩ እንዲንቀሳቀሱ የጸጥታ ኃይሉ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።
በአዲስ አበባ የጸጥታ ሥራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ የገለጹት ኮማንደር ፋሲካ፤ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ ወደሚኖርበት አገር ሲመለስ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውነታውን በማሳወቅ አምባሳደር እንዲሆንም ይፈለጋል ብለዋል።
ይሁንና አጋጣሚውን ተጠቅመው ዳያስፖራው ላይ ዝርፊያና መሰል ህገ-ወጥ ተግባር ለመፈጸም የሚሞክር ቢኖር ኮሚሽኑ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።
Via: EBC
ዋሽንግተን ዲሲ — VOA Amharic
አንድ ሚሊዮን ተጓዥ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመጭው የገና በዓል የአውሮፕያኑ አዲስ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አድርጓል፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያና ትውልደ ኢትዮጵውያንም ጥሪውን ተቀብለው ወደዚያው ለመጓዝ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አጋር ሆኖ የማስተባበር ኃላፊነት መውሰዱን ዋሽንግተን ነዋሪ የሆኑት የምክር ቤቱ ቦርድ ሰብሳቢ ካፕቴን አብይ ገ/ህይወት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡ በእንግሊዝ ለንደን ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑትን አቶ አለባቸው ደሳለኝም አነጋጋረናል፡፡
ጥሪው ያለምንም እቅድ በድንገት የተላለፈ በመሆኑ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገሮች በጥድፊያ ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑንም አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።