Home Donation Health Facility Restoration Plan for Amhara and Afar Regions

Health Facility Restoration Plan for Amhara and Afar Regions

በአማራ እና በአፋር ክልል የጤና ተቋም መልሶ ማቋቋም

by Gondar City

ኢትዮጵያ የኛን ድጋፍ ዛሬ  ትሻለች!
Health Facility Restoration Plan for Amhara and Afar Regions in Northern Ethiopia!
በአማራ እና በአፋር ክልል የጤና ተቋም መልሶ ማቋቋም !

 

በአማራ እና በአፋር ክልል የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያወጣው ዘገባ ከ 9.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በእነዚህ ክልሎች 2,732 ጤና ተቋማት፣ 4 የደም ባንኮች እና 125 አምቡላንሶች በግምት ወደ 40 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ ተዘርፈዋል፤ ወድመዋል ወይም ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል። ህዝቡ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ በስነ ልቦና ጉዳት እና በኢኮኖሚ  ውድመት ምክንያት ሙሉ በሙሉ የጤና አገልግሎት አጥቷል።

በጦርነቱ የተጎዱትን የጤና ተቋማት ወደ ነበሩበት ለመመለስ እና ለማደስ ፕሮጀክት ኪውር (Project C.U.R.E) የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ግምቱ 18 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን አምስት ሺ አዲስ የሆስፒታል አልጋዎች እና ፍራሾችን፤ ከተጨማሪ የድንገተኛ ህክምና ቁሳቁሶች ጋር ለመለገስ ሃምሳ በአርባ (50×40) ጫማ ኮንቴይነሮችን አቅርቧል። በአንድ ኮንቴነር $22,000 ዶላር የመጓጓዣ እና የማጠራቀሚያ ወጪ ያስፈልጋል። ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የመጎጎዣና የጉምሩክ ቀረጥ ደግሞ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር  በሃላፊነት ተረክቦ ለተጎዱ አካባቢዎች ያሰራጫል።

እነዚህን 50ዎቹን ኮንቴነሮች በተቻለ ፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ 1.1 ሚሊዮን ዶላር በአስቸኳይ መሰብሰብ ይኖርብናል። ይህ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ድጋፋችን የምናሳይበት  እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ፅናት ያለንን አክብሮት የምናሳይበት መልካም ተግባር ነው።

ስለዚህ ለወገን ችግር ፈጥኖ ደራሽ ወገን ነውና ለዚህ የነፍስ አድን ጥሪ ና ትብብር ሁላችንም የበኩላችን አስታዎጻኦ አንድናበረክት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ ዙም(ኦንላይን)  ታህሳስ 10 ቀን, 2014ዓ.ም.  በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ስዓት (December 19, 2021 at 12:00 NOON EST ላይ አንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳና ተናጋሪ ዶ/ር ሊያ ታደስ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ናቸው።

You may also like