264
ዋሽንግተን ዲሲ — VOA Amharic
አንድ ሚሊዮን ተጓዥ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመጭው የገና በዓል የአውሮፕያኑ አዲስ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አድርጓል፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያና ትውልደ ኢትዮጵውያንም ጥሪውን ተቀብለው ወደዚያው ለመጓዝ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አጋር ሆኖ የማስተባበር ኃላፊነት መውሰዱን ዋሽንግተን ነዋሪ የሆኑት የምክር ቤቱ ቦርድ ሰብሳቢ ካፕቴን አብይ ገ/ህይወት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡ በእንግሊዝ ለንደን ከአስተባባሪዎች አንዱ የሆኑትን አቶ አለባቸው ደሳለኝም አነጋጋረናል፡፡
ጥሪው ያለምንም እቅድ በድንገት የተላለፈ በመሆኑ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገሮች በጥድፊያ ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑንም አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።